27 የወንድ ልጅ የእርጅና ምልክቶች…ያዝናናዎታል !!

የወንድ ልጅ የእርጅና ምልክቶች !!

1. ደረት ኪስ ውስጥ እቃ ማስቀመጥ ከጀመረ፤
2. እስክሪብቶ ይዞ መዞር ከጀመረ፤
3. እየደጋገመ ቀበቶውን ማስተካከል ከጀመረ፤
4. ረጃጅም ከልሲ ማድረግ ከጀመረ፤
5. ዝርዝር ብር ዋሌት ውስጥ ማስቀመጥ ከጀመረ፤
6. ቆዳ ጫማ ብቻ ማድረግ ከጀመረ፤
7. ያለፈበት ጋዜጣ ማንበብ ከጀመረ፤
8. ታክሲ ውስጥ መስኮት ዝጉልኝ ማለት ከጀመረ፤
9. ሸሚዝ ውስጥ ቲሸርት ማድረግ ከጀመረ፤
10. የመስሪያ ቤት እድር አባል መሆን ከጀመረ፤
11. ጺሙ ሳይድግ መላጨት ከጀመረ፤
12. “እስኪ አትረብሹ!” ማለት ማዘውተር ከጀመረ፤
13. ቤቱን ደማቅ ቀለም ማስቀባት ከጀመረ፤
14. ከረምቡላ ቤት መሄድ ከጀመረ፤
15. ጃኬት ለብሶ ለቅሶ ቤት መሄድ ከጀመረ፤
16. ልብስ ሲገዛ ”ኮተን ነው?” ብሎ መጠየቅ ከጀመረ፤
17. ከ 2-ሰዓት ዜና በፊት እራቱን መብላት ከጀመረ፤
18. ሸሚዙን መስመር እስኪሰራ መተኮስ ከጀመረ፤
19. ፍንዳታ ሲያይ ደሙ መፍላት ከጀመረ፤
20. የአፍንጫ ውስጥ ፀጉሩን ለመቁረጥ መሞከር ከጀመረ፤
21. የሴት ልጅ ውበቷ ፀጉሯ ነው ማለት ከጀመረ፤
22.”ፈረንጆች ምን ይላሉ መሰለህ?” ብሎ ወሬ ከጀመረ፤
23. ካላንደር ቤት ውስጥ መስቀል ከጀመረ፤
24. የስብሰባ ኮፍያና ቲሸርት በእረፍት ጊዜው መልበስ ከጀመረ፤
25. ዘመኑን መውቀስ ከጀመረ፤
26.ስሙን ከነአያቱ መናገር ከጀመረ፤ እና
27. ይሄን ጽሁፍ ካነበበ በኋላ ”ኤዲያ ድስኩራም” ማለት ከጀመረ …… በቃ ይሄ ሰው እያረጀ ነው ማለት ነው !!
************
– (የቴዲ ጌታቸው ትዝብቶች)