የሴት ልጅ የእርጅና ምልክቶች

By Remzi Akibaw 

=======================
(ይሄን ርዕስ ስታይ ድንግጥጥጥጥ ካለች
1 ዘውትር የማለዳ ፀሃይ መሞቅ ከጀመረች፤
2 «ስለወንዶች ለኔ አትነግሩኝም» ማለት ከጀመረች፤
3 ቦርሳዋን ይዛ መፀዳጃ ቤት መግባት ከጀመረች፤
4 ከአንድ የኮስሞቲክስ ሱቅ ብቻ መግዛት ከጀመረች፤
5 ባስ ለመግባት መጋፋት ከጀመረች፤
6 የአባይና የጣናን ውሃ ስታይ «አይ ፍልውሃ ቢሆን ?!» ማለት ከጀመረች፤
7 «ሰው የተፈጠረው ከውሃ ከአፈርና ከቁም መስታውት ነው» ብላ ማሰብ ከጀመረች፤
8 ወንዶች ከአንድ በላይ ማግባት እንደሚችሉ የደነገገውን የኬኒያ ህግ ማብሰልሰል ከጀመረች፤
9 ፀጉሯን ሹሩባ ከምትሰራ መላጨትን ከመረጠች፤
10 «እማዬ ሂጂ ከኋላ እደርስብሻለሁ» ማለት ከጀመረች፤
11 «ከወንዶች ጋር ጥሩ የሆነ ሪሌሽን አለኝ» ማለት ከጀመረች፤
12 ብቻዋን ክትፎ ቤት መግባት ከጀመረች፤
13 ጨርቅ ሱሪና ካልስ በነጠላ ጫማ መልበስ ከጀመረች፤
13 «ዋናው ውስጣዊ ውበት ነው» ማለት ከጀመረች፤
14 ከአባቷ ጋር ከመሳሳቅ ወደመወያየት ከተቀየረች፤
15 «ስራ ከምፈታ……» ማለት ከጀመረች፤
17 የትንሽ ወንድሟ መግዘፍ ያስጨንቃት ከጀመረች፤
18 ለቤት ዕቃዎቿ ትልቅ አክብሮት መስጠት ከጀመረች፤
19 በተስፋ መኖርን ትታ በትዝታ መስመጥ ከጀመረች፤
20 ታክሲ ውስጥ ለእድሜ እኩዮቿ ቦታ ካለቀቅኩ ብላ መገልገል ከጀመረች፤
21 «ወንድ ልጅኮ የዋህ ነው» ማለት ከጀመረች፤
22 የቅርብ ጊዜ ካንገቷ በላይ ጉርድ ፎቶዎቿን ከማሳየት ካንገቷ በላይ መጎረድን ከመረጠች፤
23 ፌስቡክ መጠቀም ከጀመረች
24 ፊቷን በመስታውት ሳታይ ከወጣች ፊቷን ጥላው የወጣች ያህል መሰማት ከጀመራት፤
25 ውድና የሚያምሩ ጥላዎችን መያዝ ካዘወተረች፤
26 በመንገድ ከቆንጆ ሴቶች ጋር ስትተላለፍ ዙራ ማየትን ከረሳች፤
27 ደጋግማ ስለፔሬድ ማውራት ከጀመረች፤
28 የወንድ ልጅ ሚስኮል መመለስ ከጀመረች፤
29 «ስለ ስራ ጉዳይ ብናወራ…» ማለት ከጀመረች፤
30 ዱቄት ላይ በፊቷ የወደቀች እስክትመስል የፊት ፓውደር ማብዛት ከጀመረች……
:
:
31 ይሄን ሁሉ ካነበብሽ በኃላ የመጨነቅና የመደናገጥ ስሜት ከተሰማሽ… በቃ አልቆልሻል ማለት ነው…!!
:
:
32 የላይኛውን 31ኛውን አንብበሽ «ተደናግጫለሁ እንዴ ?» ብለሽ ራስሽን ከጠየቅሽ… በቃ ቻው……!!
:
ትዳር ካለሽ ባልሽ ሌላ ሴት እንዳያይ መጠባበቅ ጀምሪ ወይም አይኑን አጥፊው……… በውበትሽ:
ትዳር ከሌለሽ ጊዜው እየረፈደ ነውና እንደኔ ያለውን «ሱፐርማን» መጠባበቅ አቁመሽ የተገኘውን አግቢ !! ;-