እንደምነሽ?

እንደምነሽ?
========
እንደምነው ዓይንሽ ጥቁር እና ነጩ
እንደጊዜው መንግስት ሕዝብ አበጣባጩ.
እንደምነው ጡትሽ እንደጦር የቆመው
እንደጊዜው ምርጫ የተጭበረበረው.
እንደምነው ጭንሽ የሚወዛወዘው
እንደ ህዝብ ንብረት የሚበዘበዘው።
እባክሽ ንገሪኝ ወገብሽ እንዴት ነው?
እንደ ጋዜጠኛ ሲታሰር የኖረው። .
እኔ እንዳለሁ አለሁ እቴ ምን ጎሎብኝ
የማይመጣ ባቡር ቆሜ እየጠበኩኝ
ኔትወርክ ለሌለው ስልክ ካርድ እየገበርኩኝ
ለማይመጣ ውሃ ቧንቧ እየተከልኩኝ
ለማይበራ መብራት ደሞዝ እየላኩኝ
ለሎተሪው ቤቴ እያጠራቀምኩኝ አለሁ እንደተውሽኝ ። .
እየውልሽ እቴ የዘንድሮ ኑሮ ሆነልሽ አስፈሪ
ድንገት ተገጣጥመው ግንቦት ስላሴና የሆነ አሸባሪ
“መብራት የለም” ያለው እየተፈረጀ
“ውሃ የለም” ያለው እየተፈረጀ
“ኔቶርክ የለም” ያለው እየተፈጀ
ዘብጥያ ተጥሎ ስንት ወጣት አረጀ.
አሁን እሱን ትተሽ እንቺ እንደምን አለሽ? .
እንደምነው ፀጉርሽ ንፋስ የበተነው
እንደ ግል ፓርቲዎች የተዝረከረከው
^
ንገሪኝ እንዴት ነው?

ይመቻችሁ ~~~ ^ የተመቸው ሼር ያደርጋል::