አገር ማለት

አገር በታሪክ በቋንቋ በሀይማኖት በልምድ በተስፋ በደስታና በመክራ ተሳስሮ የሚኖር አንድ ወገን የሆነ ሕዝብ የሚኖርበት የዓለም ክፍል ነው:: አገር ማለት አያት ቅድም አያት የትወለዱበት አድገውም በጀግንነት ከውጭ ጠላት እየትከላከሉ ለሕዝብና ለመንግስት የሚጥቅም ሥራ ሠርትው እድሜያቸው ሲደርስም ልጆቻችውን ተክተው የተቀበሩበት ጉድጓድ ነው:: በመወለድ እትብት በመሞት አካል ከአፈሩ ጋራ ስለ ሚዋሐዱ የአገሩ አፈር ሕዝብ በላዩ የሚኖርበት ማለት ነው:: እግዚአብሔር ከምድርዋ ፍሬ ሕይወት እንዲጋኝባት በማድረጉ አገር እየጠባች የምታሳድግ ፍቅርዋ በአጥንት በሥጋ ገብቶ የማይደመሰስ የሆንች እናት ማለት ነው:: ከልጅነት ጀምሮ ወንዙን ተራራውን ሜዳውን ቆላውንና ደጋውን በማየት ስለ ማደግ አባቶች በሕህወትና በሞት የሥሩበት ደግ ሥራ በአእምሮ ታትሞ ስለ ቀረ በአገር እስካሉ ሲታይ በስድት ሲሆኒ ሲታሰብ ፍቅርና ናፍቆት የሚያሳድር አገር ነው:: አገር አባት እናት ዘመድ ምግብ ጌጥና ሀብት በመሆኑ ድህንትና ጥቃት በመጣ ቁጥር እስካ ሞት ድረስ እንዲሠራበት ከአያት ከቅድም አያትና ከአባቶች በጥብቅ የተሰጠ ያደራ ገንዘብ ነው::

ከታሪክና ምሳሌ (3 ኛ ምጽሐፍ)