ሰው ወዶ አይስቅም!

ሰው ወዶ አይስቅም!የዞን 9 አባላትና ጋዜጠኞቹ በሚያሳዝን ሁኔታ የሚጽፉ እጆቻቸው በሰንሰለት ታስረው አራዳ ምድብ ችሎት በቀረቡበት ወቅት ነው….ሁላችንም ችሎቱን ገብተን መከታተል እንደማንችል በመገለጹ በዝግ ሂደቱ ሲታይ በነበረበት ወቅት አንድ ነጭ ወደ ፖሊሶቹ ጠጋ ብሎ መግባት ይችል እንደሆነ ይጠይቃል፡፡ ፖሊሱ ግን መግባት እንደማይችል ከማስረዳት ይልቅ ፈጥኖ ሰውዬውን በኃይል ይገፈትረው ጀመር፡፡ በዚህ ጊዜ ነጩ ሰውዬ ቆጣ ብሎ፣ <<Oh, I am a diplomat>> ይለዋል፡፡
ዲፕሎማት የራሱ የሆነ ክብር እንዳለው በማሰብ ይመስለኛል፡፡ ፖሊሱ ግን እንግሊዝኛው የገባው አይመስልም፡፡ እናም፣ ‹‹ቀጥል ዝም ብለህ እዚህ ዲፕሎማ የለም!›› ሲለው ያ ሁሉ በውጥረት የነበረው ሰው በአንዴ አውካካ፡፡ ሰው መቼስ ወዶ አይስቅ!
እስኪ እባካችሁ ፖሊሶቻችን ተገቢውን እውቀት እንዲጨብጡ አድርጉልን ከማለት ውጭ ምን እንላለን! መቼም እውቀት ያለው ሰው በወገኑ ላይ እምብዛም አይጨክንም፤ የአምባገነኖች መሳሪያም አይሆንም ብዬ አስባለሁ!
#Freejournalists #Freezone9ers!